አረሳት ኢትዮጵያን በእርፈ መስቀል
አባ ተክለሃይማኖት ሰባኪ ወንጌል
የእግዚአብሔር ሰው ነው ተወዳጅ በ ሰማይ
የተረማመደ በጽድቅ አደባባይ
ፈውስና ጸሎቱ ቃሉ የተሰማ
ወንጌል የሰበከ በገጠ ከተማ
የእቲሳው ኮከብ የደብረ አስቦቱ
ለወንጌል ተዋጋች ንጽህት ሕይወቱ
አዝ= = = = =
ፋናው እስከ ዛሬ ሲያበራ የኖረ
የእቲሳው አባት ፍስሐጽዮን
እግዚአርያ እናቱ ማህፀነ ብሩክ
ወለደች ኮከብን ሲኦልን የሚያውክ
አዝ= = = = =
ዲያቢሎስ እስካሁን ስሙ ሲጠራበት
ሲረገጥ ይኖራል በእሳት ሰንሰለት
አዲስ ሐዋርያ የኢትዮጵያ አባት
ደጋ ና ቆላውን በመስቀል ባረካት
አዝ= = = = =
ምንጩና ፏፏቴው ተራራው ቅዱስ ነው
የአባታችን መስቀል ጽኑ ስለነካው
የተራመደበት የዳሰሰው ሁሉ
ድውይ ይፈውሳል ሳርና ቅጠሉ
