ዘጠኝ ሰዓት ሲሆን አባት ሆይ
በመስቀል ሆነህ አባት ሆይ
ድምፅህን በማሰማት አባት ሆይ
ነፍስህን ሰጠህ አባት ሆይ
ከዋክብተ ሰማይበሙሉ ረገፉ
ጨረቃና ፀሐይ ደምን አጎረፉ
ብርሃናት ጨለሙ ጠፍተው ተለያዩ
ሥጋህ በመስቀል ላይ ተጋልጦ ስላዩ
አዝ= = = = =
ጌታችን ክርስቶስ በመስቀል ላይ ሳለ
አሰምቶ ጮኸ ተጠማሁ እያለ
ማርና ወተትን ለሚመግበው
ሐሞት አመጡለት ይቅመሰው ብለው
አዝ= = = = =
አካሉ ሲወጋ ውኃ ደም ፈሰሰ
በምድር ተረጭቶ ዓለምን ቀደሰ
የገሊላ ሴቶች ዋይ ዋይ ሲሉልህ
ለእነርሱ አሰብክ እንጂ ላንተስ አላሰብክ
አዝ= = = = =
እናቱ ስታለቅስ በመስቀል ሥር ሆና
ዮሐንስን ሰጣት ጠብቆ አንዲያጽናና
መላእክትም ታዩ አጋንንትም ሸሹ
የአይሁድ ሠራዊት ፈርተው ተረበሹ
