ተወዳጅ ልጅሽን ህማሙን ስታይ
ማሰብ ይሳነኛል የአንቺን ስቃይ
በእሾህ አክሊል ጉንጉን የቆሰለ ራሱንን
በብዙ ግርፋት/የታመመ አካሉ/(፪)
በዕፅ መስቀሉ የወረደ ደሙ
የቀራንዮ ግፍ እጅግ ማስገረሙ
ደጉ ልጅሽ ታስሮ የፍጥኝ ሲሰቃይ
ተሰክቶ ቀረ/ዓይንሽ ወደ ሰማይ/(፪)
ስለመሰቀሉ አይሁድ ሲደሰቱ
ሲስቁ ሲያሾፉ ቁማር ሲጫወቱ
ሲዘባበቱበት አይንሽ በማየቱ
ህሊናሽ ተገርፏል/በሀዘን በብርቱ/(፪)
ብላቴናይቱ የዳዊት ልጅ ማርያም
ስለደረሰብሽ ቢነገር አያልቅም
ተጠማው ቢላቸው መፃፃ አስጎነጩት
መርገም አስወግዶ/ቢሰጣቸው ሕይወት/(፪)
ለመጠጡ እንዲሆን መፃፃ ከሐሞት
ሰፍነግን ጨምረው በዘንግ አስጎነጩት
ዳዊት በትንቢቱ እንደተነበየው
በምግቤ መራራን/ጨመሩ እንዳለው/(፪)
ይኄ ሁሉ ሲሆን ድንግል ተመልክታ
መፅናናት ተሳናት በሐዘን ተነክታ
ኤሎሄ ኤሎሄ ጌታ ባለ ጊዜ
እጅግ ኃያል ነበር/የማርያም ትካዜ/(፪)
