በየገዳማቱ በየበረሃው ውስጥ
ስለተሰደዱት ፍቅርህን በመምረጥ
የዓለም ውዳቂ ምናምንቴ ሆነው
ስለ ፍቅርህ ሲሉ ክብራቸውን ትተው
/እግዚአብሔር ሆይ ማረን/(፪)

የዓለም ውዳቂ ጉድፍ በተባሉት
በምድር እየኖሩ በጽድቅ ሕይወት ባሉት
ዓለም አና አምሮቷን ትተው በመነኑት
/ኢየሱስ ሆይ ማረን እግዚአብሔር ሆይ ማረን/(፪)
አዝ= = = = =
ሕያዋን በሆኑት እስከ ዘለዓለም
ከኢየሱስ ጋራ ሞተው በመስቀል ዓለም
ዓለም የናቃቸው እነርሱም የናቁት
/አምላክ እራራልን አትጨክን በእውነት/(፪)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back To Top ➤