“እግዚአብሔር በቃሎቹ የታመነ ነው፥ በሥራውም ሁሉ ጻድቅ ነው፤ እግዚአብሔር የተፍገመገሙትን ሁሉ ይደግፋቸዋል፥ የወደቁትንም ያነሣቸዋል።” መዝ 145 ፥ 14
“እግዚአብሔር በመንገዱ ሁሉ ጻድቅ ነው በሥራውም ሁሉ ቸር ነው።” መዝ 145 ፥ 17
” እግዚአብሔር ለሚጠሩት ሁሉ፥ በእውነት ለሚጠሩት ሁሉ ቅርብ ነው።
ለሚፈሩት ምኞታቸውን ያደርጋል፥ ልመናቸውንም ይሰማል ያድናቸዋልም።
እግዚአብሔር የሚወድዱትን ሁሉ ይጠብቃል፤ ኃጢአተኞችንም ሁሉ ያጠፋል።” መዝ 145 ፥ 18 – 20
“አቤቱ፥ ውኆች አዩህ፥ ውኆችም አይተውህ ፈሩ፤ ጥልቆች ተነዋወጡ፥ ውኆችም ጮኹ።” መዝሙር 77 ፥ 16
“አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ ፥ እጅግ ደስ ይበልሽ ፤ አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ ፥ እልል በዪ ፤ እነሆ ፥ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው ፤ ትሑትም ሆኖ በአህያም ፥ በአህያይቱ ግልገል በውርንጫይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል።” ዘካርያስ 9 ፥ 9
“እግዚአብሔርም ፦ ይህ በር ተዘግቶ ይኖራል እንጂ አይከፈትም ፥ ሰውም አይገባበትም የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ገብቶበታልና ፥ ተዘግቶ ይኖራል።” ሕዝቅኤል 44 ፥ 2
“ነገር ግን ከእናንተ ማንም በኃጢአት መታለል እልከኛ እንዳይሆን ፥ ዛሬ ተብሎ ሲጠራ ሳለ ፥ በእያንዳንዱ ቀን እርስ በርሳችሁ ተመካከሩ ፤ የመጀመሪያ እምነታችንን እስከ መጨረሻው አጽንተን ብንጠብቅ ፥ የክርስቶስ ተካፋዮች ሆነናልና” ዕብራውያን 3 ፥ 13
“እግዚአብሔር ትዕግሥተኛ ፥ ኃይሉም ታላቅ ነው ፥ ንጹሕም በእርሱ ዘንድ ንጹሕ አይደለም ፤ እግዚአብሔር በወጀብና በዐውሎ ነፋስ ውስጥ መንገድ አለው ፥ ደመናም የእግሩ ትቢያ ነው።” ናሆም 1 ፥ 3
“ገብርኤል ሆይ ፤ ስለእኔ ሕይወቱን አሳልፎ የሰጠውን ፈጣሪ ‘በአርአያህና በአምሳልህ የፈጠርከውን እንዴት ታጠፋዋለህ? አሳምረህ ያነፅከውንስ ሕንፃ ስለምን ታፈርሰዋለህ?!’ እያልክ ማልድልኝ ” መልክአ ገብርኤል
“‘እኛ እንዳንጠፋ እግዚአብሔር ተመልሶ ይጸጸት እንደ ሆነ ፥ ከጽኑ ቍጣውም ይመለስ እንደ ሆነ ማን ያውቃል?’ እግዚአብሔርም ከክፉ መንገዳቸው እንደተመለሱ ሥራቸውን አየ ፤ እግዚአብሔርም ያደርግባቸው ዘንድ በተናገረው ክፉ ነገር ተጸጽቶ አላደረገውም።” ዮናስ 3 ፥ 9
